የወልድያ ኤፍ ኤም 89.2 የተመሰረተበት ቀን

የወልድያ ዪኒቨርስቲ ማበረሰብ ተኮር ኤፍ ኤም 89.2 የተመሰረበትን 2ኛ ዓመት ክብረ በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት አክብሯል ፡፡
በክብረ በዓሉም የሬዲዮ ጣቢያዉ ስራ አስኪያጅ አቶ ኪዳነ ማሪያም ጌታሁን ጣቢያዉ በሁለት አመት ቆይታዉ ህብረተሰቡን የሚያስተምሩ የሚያዝናኑ እንዲሁም መረጃ የሚሰጡ ፕሮግራሞች የተሰራጩበት መሆኑን ገልጸዉ የተለያዩ ዉጣ ዉረዶች ቢገጥሙም በድል የታለፉ መሆኑን አብራርተዋል ፡፡
በቀጣይም ሬዲዮ ጣቢያዉ የአድማጮችን ፍላጎት መሰረት ያደረጉ እና የህብረተሰቡን የመረጃ ጥማት ለማርካት ተደራሽነቱንና ጥራቱን በማስፍት በአዳዲስ ፕሮግራሞች ወደ ህብረተሰቡ እንደሚደርስ ስራ አስኪያጁ ጠቁመዋል ፡፡
የሬዲዮ ጣቢያዉ የሁለት አመት ቆይታ የተሳካ እንዲሆን የበኩላቸዉን ለተወጡ የዩኒቨርስቲከዉ ማህበረሰብ ፣ የጣቢያዉ ሰራተኞች፣ ለአጋር አካለት እና ለተከበሩ የወልድያ ኤፍ ኤም 89.2 ሬዲዮ አድማጮች በሬዲዮ ጣቢያ ስም ስራ አስኪያጁ የላቀ ምስጋና አቅርበዉ በቀጣይም ከጎናቸዉ እንዲቆሙ ጥሪ አስተላልፈዋል ፡፡
Scroll to Top